Photo Gallery

Photo Gallery admin August 24, 2023
የስዊስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያን (SDE) ዶ/ር ሊያ ታደሰ በይፋ መርቀዉ ጉብኝት አድርገዋል።

የስዊስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያ በዘመናዊ የምርመራ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን በሀገሪቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው የተሟላ የፓቶሎጂና የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎትን በመስጠት ለኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለመድረስና በርካቶች ወደ ዉጭ ለመሄድ ወይም ናሙና ለመላክ የሚገደዱባቸዉን ምርመራዎች እዚሁ በጥራት ለመስጠት ያለመ ነው። መ‍ሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ በሆነ መልኩና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በተደገፈ መልኩ ላቦራቶሪዉ እንደ CBC፣ LFT፣ Lipid እና RFT ካሉት መሰረታዊ የክሊኒካዊ የላቦራቶሪ ምርመራዎች አንስቶ ለአጥንት እና የመገጣጠሚያዎች ምርመራዎች፣ የልብና የካንሰር ምርመራዎች/ማርከሮች፣ መካንነት፣ የደም መርጋት፣ የሆርሞን ዳሰሳዎች፣ የበሽታ መከላከያ ዘዴዎች ምርመራ ድረስ ብዙ አይነት ምርመራዎችን ያጠቃልላል። ሂስቶፓቶሎጂ፣ ሳይቶፓቶሎጂ፣ ፈሳሽ ላይ የተመሰረተ ሳይቶሎጂ (LBC)፣ ዲጂታል ፓቶሎጂ፣ ቴራፒዩቲካል መድሐኒት መላመድ ምርመራዎች (AMR) እና ሌሎችንም ምርመራዎች እጅግ ዘመናዊ በሆኑ መሳሪያዎችና ባጠረ ጊዜ የሚሰጥ መሆኑን ማየታቸዉ ዶ/ር ሊያ እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዋል።